ቀጥታ፡

የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ከአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ሰመራ ሚያዚያ 9/2014 (ኢዜአ) የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ከአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሃት ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ የሚውል የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።


የአፋር ክልል ፍይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ደርሳ መሀመድ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንዳሉት በክልሉ በአሸባሪው ህወሀት ቡድን ወረራ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ደርሷል።

ቡድኑ በፈጸመው ወረራና ግፍ ካለው የተፈናቃይ ወገኖች ቁጥር አንጻር በመንግስት አቅም ብቻ የሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ የማይቻል መሆኑን አመልክ


የአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ፎረም በክልሉ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ላበረከተው ድጋፍ በተጎጂ ወገኖች ሰም አመስግነዋል።

ድጋፉን ያስረከቡት በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ፎረም ሰብሳቢ ዶክተር ተፈሪ መላኩ በበኩላቸው "የአፋር ህዝብ ለሀገሩ  ሉአላዊነትና ክብር የከፈለው ውድ መስዋእትነት በታሪክ ሲታወስ የሚኖር ነው" ብለዋል።


በሽብር ቡድኑ ወረራ ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ንጹሃን አርብቶ አደሮች የከፋ ግፍ እንደተፈጸመባቸውና  ሃብትና ንብረታቸው መዘረፉን መገንዘባቸውን ተናግረዋል።  

"ጉዳት የደረሰባቸው የኢትዮጵያ እውነተኛ የቁርጥ ቀን  ልጆችን መደገፍ የሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ግዴታ ነው" ብለዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ግዴታቸውን ለመወጣት በተለያዩ ጊዚያት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ  ሰብአዊ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰው ፎረሙ በዛሬው እለትም የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን  ገልጸዋል።

ፎረሙ በቀጣይም ከሰብአዊ እርዳታ ባለፈ በመልሶ ማቋቋም ተግባር ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ሃላፊነቱን እንደሚወጣ ዶክተር ተፈሪ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም