ቀጥታ፡

ተመድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ6 የአፍሪካ ሀገራትና ለየመን 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

ሚያዝያ 09 ቀን 2014 (ኢዜአ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ አቅርቦቱ በኩል በኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማልያ፣ ሱዳን፣ ናይጄሪያ፣ ኬኒያና የመን ለችግር የተጋለጡ ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል ድጋፍ ይፋ አድርጓል።

የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበርያ (ኦቻ) ቃል አቀባይ ጄንስ ላርኬ ለቪኦውኤ እንደገለጹት በሀገራቱ የተደቀነውን ዘርፈ ብዙ ችግርና የረሃብ አደጋ ለመቋቋም ድጋፍ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኗል።

በዚህም ተመድ ለእያንዳንዱ ሀገራት የሚሆን 43 ሚሊዮን ዶላር ከለጋሾች መጠየቁን አስታውሰው ተመድ በራሱ ለአስቸኳይ የአደጋ ጊዜ መቋቋሚያ የሚሆን 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።

ድጋፉ የተደረገው ኮቪድ-19፣ ድርቅ፣ ግጭቶችና የኢኮኖሚ መናወጦች በፈጠሩት ቀውስ በሀገራቱ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎች ለከፍተኛ ችግር በመጋለጣቸው ነው።

በሩስያና በዩክሬን መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ችግሩን በማባባሱም አሁኑኑ መፍትሄ መፈለግ ስለሚያሻው ድጋፉ ተደርጓል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም