የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናትና የክልል ርአሰ መስተዳደሮች በደብረ ብርሃን ከተማ የሚካሄዱ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው

100

ሚያዚያ 09 ቀን 2014 (ኢዜአ) የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናትና የክልል ርእሰ መስተዳደሮች በደብረ ብርሃን ከተማ የሚካሄዱ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝቱ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህና የህዝብ ተካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎን እንዲሁም የተለያዩ ክልሎች ርእሰ መስተዳደሮች ተገኝተዋል።

በደብረብርሀን ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪና ኢቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ ብርሀን ገብረህይወት በወቅቱ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደብረ ብርሃንና አካባቢው በኢንቨስትመንት ተመራጭ እየሆነ መጥቷል።

ዘንድሮ 16 ቢሊዮን ብር ላስመዘገቡ 50 ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም የኢንቨስትመንት ቦታ ከወሰዱት 330 ነባር ፕሮጀክቶች ውስጥም 52 የሚሆኑት ግንባታቸውን አጠናቀው ወደ ማምረት መሸጋገራቸውን አስረድተዋል።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ከፍተኛ አመራሩ በደብረ ብርሃን አካባቢ የሚገኙ የጠርሙስ፣ የመድሃኒትና ሌሎች ፋብሪካዎችን እየጎበኙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም