ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው የተጓዙ 50 ከባድ ተሽከርካሪዎች መቀሌ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው የተጓዙ 50 ከባድ ተሽከርካሪዎች መቀሌ ገቡ
ሚያዚያ 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) ሰሞኑን ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው የተጓዙ 50 ከባድ ተሽከርካሪዎች በሰላም መቀሌ መግባታቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ በትዊተር ገጹ እንዳስነበበው፤ ተሽከርካሪዎቹ ወሳኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ጭነዋል።
ከጫኑት ውስጥ ስንዴ፣ የቅባት እህልና ነዳጅ እንደሚገኝበት ጠቁሟል።