የኢዜአን የ80 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ አውደ ርዕይ በሀዋሳ ተከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
የኢዜአን የ80 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ አውደ ርዕይ በሀዋሳ ተከፈተ
ሀዋሳ ፤ ሚያዝያ 7/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት(ኢዜአ) የተመሰረተበት 80ኛ ዓመት በማስመልከት የተዘጋጀ የፎቶና ቪዲዮ ዓውደ ርዕይ በደቡብና ሲዳማ ክልሎች ደረጃ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተከፈተ።
ዓውደ ርዕዩን መርቀው የከፈቱት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ አቶ ተሰማ ዲማ፣ የሲዳማ ክልል ፕሬስ ሴክሬተርያት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍሊጶስ ናሆም ፣ የደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሰናይት ሰለሞን እና የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ሀብቴ ከኢዜአ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ ጋር በመሆን ነው።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ተገኝተዋል።
ለሶስት ቀናት የሚቆየው ዓውደ ርዕዩ ኢዜአ ባለፉት 80 ዓመታት ሲገለገልባቸው የነበሩ መሳሪያዎችና ፎቶ ግራፎች ለዕይታ ከቀረቡት መካከል ይገኙበታል።
ኢዜአ ባለፈባቸው ዓመታት አስተማማኝ የዜና ምንጭ በመሆን መረጃ ለመገናኛ ብዙሃን በማቀበል የነበረውና በቀጣይ በሚኖረው ሚና ላይ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።