ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በኋላ በአስመራ ዳግም ኤምባሲዋን ከፈተች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በኋላ በአስመራ ዳግም ኤምባሲዋን ከፈተች
አዲስ አበባ ጳጉሜ 1/2010 ኢትዮጵያ ላለፉት 20 ዓመታት ዘግታው የቆየችውን በኤርትራ የሚገኘው ኤምባሲዋን ዛሬ በይፋ ከፈተች። ኤምባሲው የተከፈተው በኤርትራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተገኙበት ስነ-ስርዓት ነው።
ኢትዮጵያና ኤርትራ በመካከላቸው ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ሳቢያ ግንኙነታቸው ላለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ተቋርጦ ቆይቷል። ሆኖም የአገራቱ መሪዎች በቅርቡ በወሰዱት እርምጃ ግንኙነቱን ለመቀጠል የሚያስችል ሁሉን አቀፍ ስምምነት አድርገዋል። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በተመሳሳይ የአገራቸውን ኤምባሲ በአዲስ አበባ መክፈታቸውም አንደዚሁ። ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን ከመቀጠል ባሻገር በአገራቱ መካከል የምጣኔ ኃብት፣ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና የህዝብ ለህዝብ መቀራረብን ማጎልበት የስምምነቱ አካል ነው። ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች ለመጠቀም የሚያስችላት ሁኔታም ተፈጥሯል። በትናንትናው እለትም ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የገቢ እና የወጪ እቃዎችን የጫነ አንድ የኢትዮጵያ መርከብ መልህቁን ምፅዋ ወደብ ላይ ጥሏል። የሁለቱ አገራት የወደብ የንግድ ግንኙነቱም በመሪዎች ደረጃ የተካሄደውን የአገራቱን መስተጋብር ወደ መሬት ያወረደ ነው ተብሎለታል።