ቀጥታ፡

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል 300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ

ሚያዚያ 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአለም ባንክ በኢትዮጵያ በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል 300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን አስታወቀ።

ባንኩ በአለም የልማት ማህበር በኩል ግጭት ለተከሰተባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ድጋፍ ማጽደቁን አመልክቷል።

ፕሮጀክቱ መሠረታዊ አቅርቦቶችን፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን፣ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ያካተተ መሆኑንም ባንኩ ገልጿል።

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ጾታዊ ጥቃትና የስነ ልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ እንደሚያደርግ ተነግሯል።

ፕሮጀክቱ በአገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከናወን የተገለጸ ሲሆን በዋናነት በአማራ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ትግራይ ክልሎች እንደሚተገበር ተመልክቷል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
መረጃዎቻችንን በዩቲዩብ፡-

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም