በኢትዮጵያ ከሁለት ዓመታት በፊት የተጀመረው የአቮካዶ ምርታማነት ጥረት ፍሬያማ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ

487

ሚያዚያ 03 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ከሁለት ዓመታት በፊት የተጀመረው የአቮካዶ ምርታማነት ጥረት ፍሬያማ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ራሳችንን በምግብ ለመቻል፣ በስንዴ ላይ እንዳደረግነው ሁሉ በአትክልትና ፍራፍሬ ምርታማነት ላይ ዐቅማችንን ማጠናከር አለብን” ብለዋል።

በመልዕክታቸውም ”ከሁለት ዓመታት በፊት የጀመርነው የአቮካዶ ምርታማነት ጥረት ፍሬያማ መሆኑን አሳይቷል” ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም