በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የምትታተመው "ነጋሪ" መጽሔት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን አካታ ለንባብ በቅታለች - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የምትታተመው "ነጋሪ" መጽሔት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን አካታ ለንባብ በቅታለች
ሚያዚያ 2/2014/ኢዜአ/ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የምትታተመው "ነጋሪ" መጽሔት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን አካታ ለንባብ በቅታለች።
መጽሔቷ በስፋት ከዳሰሰቻቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ እንቅስቃሴ ዙሪያ ነው።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ከመጽሔቱ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ፓርኮቹ በውጭ ምንዛሬና በስራ እድል ፈጠራ ይበል የሚያሰኝ ውጤቶች እያስገኙ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በ2014 ዓ.ም ግማሽ ዓመት ብቻ ከ104 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን አብራርተዋል።
በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሮያ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሙላቱ ፍቃዱም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በምን መልኩ ዘላቂ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
መፅሔቷ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ የተለያዩ አገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን ከዘመኑ ሁኔታ ጋር አመሳክራ ለአንባቢዎቿ ይዛ ቀርባለች፡፡
ከነዚህ መካከል 'የአገራቸው ልጆች በቁርጥ ቀን' በሚል ርዕስ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆችና ደጋፊዎች በኢትዮጵያ ላይ ሲደረግ የነበረውን ኢ-ፍትሓዊ ጫና ሲቃወሙ የቆዩበትን መንገድ በስፋት ዳሳለች።
በተመሳሳይ 'ኢትዮጵያ የጥቁሮች የነጻነት ቀንዲል' እና 'አፍሪካ 21ኛውን ክፍለ ዘመን በአድዋ ድል መንፈስ' የሚል አርዕስት ስርም ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ ክብርና ነጻነት የከፈሉትን ዋጋ የሚዳስስ ዕሁፍ ተካቷል።
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ያለፈባቸውን ውጣ ውረዶችና አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን በስፋት የሚዳስስ ጽሁፍም 'አዲስ ገጽ-አዲስ ምዕራፍ' በሚል ርእስ ተሰናድቶ ቀርቧል።
በተጨማሪም የግብርናው ዘርፉ ላይ ስር ነቀል ለውጥ በማምጣት ኢኮኖሚውን ማሻገር በሚቻልባቸው ሃሰቦች ላይ ሰፋ ያለ ዳሳሰ ይዛለች፡፡
የፆታ ጥቃት' እንዲሁም እንዲሁም የጤና ጉዳዮችም በመጽሄቱ ከተዳሰሱ ሃሳቦች መካከል ናቸው፡፡
ነጋሪ መጽሔት 20ኛ እትም በ76 ገፆች ተቀንብባ ከዛሬ ጀምሮ ለንባብ በቅታለች፡፡