የምርመራና የጥናት ቡድኑ በአፋርና አማራ ክልሎች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ እያከናወነ ያለውን ጥናት ሂደት ለሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል አቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
የምርመራና የጥናት ቡድኑ በአፋርና አማራ ክልሎች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ እያከናወነ ያለውን ጥናት ሂደት ለሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል አቀረበ
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2014 /ኢዜአ/ ከፍትሕ ሚኒስቴር፣ ከፌዴራል ፖሊስና ከመከላከያ ሚኒስቴር የተዋቀረው የምርመራና ጥናት ቡድን በአፋርና አማራ ክልሎች የተፈጸሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ እያካሔደ ያለውን ጥናት ሂደት ለሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል አቀረበ።
የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል በጦርነቱ የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ገቢራዊነት ላይ በምርመራ ቡድኑ የቀረበለትን ሪፖርት እየገመገመ ነው።
በውይይቱ በፍትሕ ሚኒስቴር፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሚኒስቴር የተዋቀረ የምርመራና ጥናት ቡድን በሁለቱ ክልሎች የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀሎች ላይ በጥናት የደረሰበትን ደረጃ አቅርቧል።
ጥናቱ እስካሁን የደረሰበት ደረጃ ጥፋተኞችን ተጠያቂ ለማድረግ በሚያስችል መልኩ መከወኑና በግምገማው መሰረትም ቀጣይ የምርመራ ስራዎችም እንደሚኖሩ ነው የተገለፀው።
ከሰብዓዊ መበት ጥሰቶችና አፈፃፀማቸውን በመመርመር ጥፋተኞችን ተጠያቂ ከማደረግ ባለፈ ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም ጥረትን ገቢራዊ ማድረግ ስለሚቻልባቸው ጉዳዮችም በሪፖርቱ በዝርዝር ተጠቅሰዋል።