ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ መድን እና ለገጣፎ ለገዳዲ እግር ኳስ ክለቦች ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላለቀሉ

መጋቢት 23/2014/ኢዜአ/ ኢትዮጵያ መድን እና ለገጣፎ ለገዳዲ እግር ኳስ ክለቦች ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላለቀሉ።

በከፍተኛ ሊጉ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ በዛሬው እለት በተለያዩ ክለቦች መካከል ተደርጓል ።

የ2014  ዓ.ም የከፍተኛ ሊግ እግር ኳስ  30 ክለቦች በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በ2015 ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ለመሆን በምድብ "ለ" እና "ሐ" በተደረጉ ጨዋታዎች ሁለቱ የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሜዳ በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስፖርት ክለብ፤ ደቡብ ፖሊስን 1 ለ 0 በማሸነፍ ከ8 ዓመታት በኋላ ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላቅሏል።

በምድብ "ለ " ከተደለደሉት ባቱ ላይ በተደረገ ጨዋታ ለገጣፎ ለገዳዲ ሰንዳፋ በኬን 4 ለ 0 በማሸነፉ  በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ሆኗል።

በምድብ "ሀ" ከተደለደሉት ኢትዮ ኤሌክትሪክ የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊነቱን አንድ ሳምንት እየቀረው ማረጋገጡ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ መድን፣ ለገጣፎ ለገዳዲ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ የ2015 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊዎች ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም