በሀገር አቀፍ ደረጃ የዓለም የሴቶች ቀን ማጠቃለያ መርሀ ግብር በባህር ዳር እየተካሄደ ነው

113

ባህር ዳር ፤ መጋቢት 23/2014(ኢዜአ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የዓለም የሴቶች ቀን ማጠቃለያ መርሀ ግብር የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተለያየ ዝግጅት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

ቀኑን ቀደም ሲል "እኔም የእህቴ ጠባቂ ነኝ" በሚል መሪ ሀሳብ በየደረጃው በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየ ሲሆን፤  የዛሬው ሀገር አቀፍ መርሀ ግበር የማጠቃለያ  መሆኑ ተመላክቷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ  ውይይት የሚደረግ ሲሆን የሴት አደረጃጀቶች እያከናወኗቸው ያሉ ስራዎች ጉብኝት እንደሚኖር ታውቋል።

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ  አለም አቀፍ የሴቶች ቀን አስመልክተው በቪዲዮ ኮንፍረንስ መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

በዝግጅቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ  የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬና የብልፅግና ፓርቲ አማራ ክልል ጽህፈት ቤት   ሃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ፣  ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት እየተሳፉ ነው።

የሴቶች ቀን ዘንድሮ   በዓለም ለ111ኛ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ  ሲከበር መቆየቱ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም