ቀጥታ፡

ለምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ጠንካራ ግንባታ አባል አገራቱ እንዲሰሩ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጠየቁ

መጋቢት 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለምስራቅ አፍሪካ ለተጠንቀቅ ኃይሉ ጠንካራ ግንባታ የተጠንቀቅ ኃይል አባል ሀገራቱ እንዲሰሩ ጠየቁ።

ለ15 ቀናት በኬኒያ ለምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ሃይል መኮንኖች ሲሰጥ በቆየው ስልጠና ማጠቃለያ ላይ ንግግር ያደረጉት የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ሃይል መሪዎች ኮሚቴ ሊቀመንበርና የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በቀጠናው የሚታየውን የጸጥታ ችግርን ለመቆጣጠር የምስራቅ አፍሪካ የተጠንቀቅ ኃይል ዝግጁ ሆኖ መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አባል ሀገራቱ ለተጠንቀቅ ሃይሉ መጠናከር እያደረጉ ላለው አስተዋጽኦ አመስግነው ኃይሉ ተጠናክሮ እንዲገነባ አባል ሀገራቱ እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ጽሕፈት ቤት ዳይሬክትር ብርጋዴር ጄኔራል ጌታቸው ሽፈራው በበኩላቸው አሁን የተሰጠው ስልጠና ኃይሉን በተጠናከረ ሁኔታ ለመገንባት እንደሚያስችል አስረድተዋል።

በስልጠናው ላይ ከኬንያ ኢትዮጵያ፣ሱዳን፣ኡጋንዳ፣ቡሩንዲ፣ጅቡቲ፣ሱማልያ፣ሲሼልስና ኮሞሮስ የተውጣጡ ወታደራዊና የሲቪል ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የምስራቅ አፍሪካ የተጠንቀቅ ኃይልን ለማጠናከርና በግንባር ቀደምትነት ለመስራት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ኬንያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ መስማማታቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም