ቀጥታ፡

በጂዳ እና አካባቢው ባሉ እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ ከ408 በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገር ቤት ተመለሱ


መጋቢት 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) በጂዳ እና አካባቢው ባሉ እስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ከ408 በላይ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ወደ ሃገር ቤት ተመለሱ።


በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ብሔራዊ አስፈፃሚ ኮሚቴ በማዋቀር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በተለያየ ደረጃ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል።


ከትላንት በስቲያ በጀመረው በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ በአንድ ቀን ከሪያድ 936 ኢትዮጵያዊን ማምጣት የተቻለ ሲሆን ዛሬ ማለዳም 393 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።


ረፋዱ ላይ ደግሞ በሁለተኛ በረራ በጂዳ እና አካባቢው ባሉ እስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ከ408 በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገር ቤት ሊመለሱ ችለዋል።


ዛሬ በሚደረጉ በረራዎች አጠቃላይ የገቡትን ጨምሮ ከጅዳ 1173 በሳኡዲ አረቢያ በእስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ዜጎች ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።


ተመላሾቹ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሀላፊዎች ተቀብለዋቸዋል።


ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም