ኢትዮጵያና ኬንያ በሠላም እና ደህንነት ለመተባበር የሚያስችል ምቹ ሁኔታና ዕድል አላቸው - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያና ኬንያ በሠላም እና ደህንነት ለመተባበር የሚያስችል ምቹ ሁኔታና ዕድል አላቸው - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
መጋቢት 21 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያና ኬንያ በሠላም እና ደህንነት ለመተባበር የሚያስችል ምቹ ሁኔታና ዕድል አላቸው ሲሉ የኢፌዲሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።
ፊልድማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ናይሮቢ ውስጥ ዛሬ ተወያይተዋል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከኬንያ አቻቸው ጄኔራል ሮበርት ኪቢቹ ጋር ባደረጉት ምክክር ሁለቱ አገሮች በሁለትዮሽ እና በአካባቢያዊ የፀጥታ ጉዳይ ለመተባበር ተስማምተዋል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያና ኬንያ በሠላም እና ደህንነት እንዲተባበሩ የተመቻቸ ሁኔታ እና ዕድል እንዳለ ገልፀዋል፡፡
ጄኔራል ኪቢቹ በበኩላቸው የረጅም ጊዜ ወዳጅ የሆኑት ኢትዮጵያና ኬንያ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ማጠናከር እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹምቹ በስልጠና፣ በሠላምና ደህንነት ማስከበር ዘርፎች ለመደጋገፍ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
ኢትዮጵያና ኬንያ አባል የሆኑበትን የምስራቅ አፍሪካ የተጠንቀቅ ኃይልን (East Africa Standby Force ESAF) ለማጠናከር በግንባር ቀደምትነት ለመስራት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ጄኔራል ኪቢቹ መስማማታቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሴ ለኢዜአ ገልጿል።