በጅማ ከተማ ማርና ቅቤን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ሲያዘጋጁ የተገኙ ዘጠኝ ግለሰቦች ተያዙ

62
ጅማ ነሀሴ 29/2010 በጅማ ከተማ ማርና ቅቤን ከባዕድ ነገር ጋር በመቃላቀል ሲያዘጋጁ ተገኝተዋል ያላቸውን ዘጠኝ ግለሰቦች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በጅማ ከተማ  የወረዳ  ሁለት ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ፋድል መሀመድ ለኢዜአ  እንደገለጹት ትናንት የተያዙት እነዚህ ግለሰቦች ድርጊቱን ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ነው፡፡ ግለሰቦቹ ድርጊቱን ሲፈጽሙ የተገኙት በከተማው ቦቾ ቦሬ ቀበሌ እና በአውይቱ መንደር ተከራይተው በነበሩበት ስምንት  ክፍሎች ያላቸው ቤቶች ውስጥ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ ባደረገው አሰሳ 44 ማዳበሪያ ማር፣ ስምንት ኬሻ ቅቤ ፣ በርካታ የታሸጉ የሞተር ዘይት፣ ሳሙና እና ሌሎች ምንነታቸው ያልታዋቁ ቁሶች አብረው መያዛቸውን አመልክተዋል፡፡ ዋና ኢንስፔክተሩ እንዳሉት በድርጊቱ ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች ተጨማሪ ምርመራ በማድረግ ለህግ ይቀርባሉ፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም