ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

መጋቢት 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጂቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝተዋል።ከጉብኝቱ በኋላ የሁለቱ አገሮች መሪዎች በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም እንደገለጹት፤ መሪዎቹ በዋናነት ኢትዮጵያና ጂቡቲ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ፣ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም በሌሎች በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም ቀጣናዊ ትስስር ስለሚጠናከርበት ሁኔታም መምከራቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም