የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከውጭ ወደ አገር ከተመለሱ የፖለቲካ ሀይሎች ጋር ውይይት አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከውጭ ወደ አገር ከተመለሱ የፖለቲካ ሀይሎች ጋር ውይይት አደረገ
አዲስ አበባ ነሀሴ 29/2010 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከውጭ ከተመለሱ የፖለቲካ ሀይሎች ጋር በዲሞክራሲያዊ ምርጫና በፖለቲካ ፓርቲ አመሰራረት ላይ ውይይት አደረገ። መንግስት ባደረገው ጥሪ መሰረት ወደ አገር የመጡ ሀይሎች በቦርዱ እውቅና አግኝተው ሰላማዊ እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የአፋር ህዝብ ፓርቲ (አህፓ)፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት)፣ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መአህድ)ን ጨምሮ ከ12 በላይ ከውጭ የተመለሱ የፖለቲካ ሀይሎች በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ምንነትና ስርዓት፣ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲ አመሰራረት ህጎች በውይይቱ ተነስተዋል። የፖለቲካ ሀይሎቹ ለውይይት መጠራታቸው እንዲሁም ምርጫ ቦርድ የሚያደርገው የለውጥ እንቅስቃሴ መልካም መሆኑን ገልፀዋል። በውይይቱም ምርጫ ቦርድ እየተቀየረ ነው ከተባለ መተማመኛችን ምንድን ነው? ክልላዊ ፓርቲ ሆኖ ለመመዝገብ የክልሉ ፈቃድ ያስፈልጋል? ሲሉ ጠይቀዋል። በተጨማሪ የምርጫ አስፈፃሚዎች ገለልተኝነትና ብቃት ላይ ጥያቄ አንስተዋል። ምርጫ አስፈፃሚዎች በተቋሙ የሰለጠኑና እነሱን የሚያሰለጥን ተቋም ቢኖር መልካም መሆኑንም ተናግረዋል። ከትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ሪፎርሞች አሉ ቢባልም በፁሁፍ የተቀመጠ መተማመኛ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡
ከአፋር ህዝብ ፓርቲ ዶክተር ኮንቴ ሙሳ በበኩላቸው "የክልል ፓርቲ ሆኖ ለመመዝገብ ከምርጫ ቦርድ የአባላት ወይም ፊርማ ማሰባሰብ ከጀመርን በኋላ ክልሎችን ማስፈቀድ ያስፈልጋል" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ከኦነግ ብርጋዴር ጄነራል ሀይሉ ጎንፋ በበኩላቸው ምርጫ ቦርድ ከታች እስከ ላይ ከወገንተኝነት ነፃ የሆኑ አባላቱን በመመደብ መስራት እንደሚተበቅበት ተናግራዋል፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ ቦርዱ ለመተማመን እየወሰዳቸው ያሉ የለውጥ እርምጃዎችን ጠቅሰዋል። የቦርዱ ከፍተኛ አመራሮች ከየትኛውም የፖለቲካ ቡድን ገለልተኛ እንደሆኑ በመጥቀስ እስከታች ያለው ምርጫ አስፈፃሚ ገለልተኛ እንዲሆን ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል። የቦርዱ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ነጋ ዱፊሳ በበኩላቸው በምስረታ ሂደት የክልሎች ፈቃድ እንደማያስፈልግ ጠቁመዋል። የምርጫ አስፈፃሚዎችን ገለልተኝነት በተመለከት ከ45 ሺህ በላይ በሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ከሩብ ሚሊዮን በላይ ምርጫ አስፈፃሚ ስለሚያስፈልግ ቋሚ ማድረግ እንደማይቻል ገልጸው ከተመለመሉ በኋላ ፓርቲዎች አስተያየት እንዲሰጡ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ፓርቲዎቹ ከዚህ ቀደም ተመዝግበው የነበሩ ከሆነ እንደገና መመዝገብ ያስፈልጋል ወይ የውጭ ዜግነት ያላቸውስ እንዴት ይሳተፋሉ የሚል ጥያቄዎችም ተነስተዋል። የቦርዱ የፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ነጋ ዱፊሳ በሁለት ምርጫ ያልተሳተፈ ፓርቲ ህጋዊነቱን የሚያጣ እንደሆነ ገልጸው ''በህግ የተደነገገው በአገር ውስጥ የፖለቲካ ተሳትፎ የሚያደርጉት ኢትዮጵያውያን ብቻ በመሆናቸው በዚህ አግባብ ይሰራል'' ብለዋል። ቀጣዩን አገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ገለልተኛና በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን ምርጫ ቦርዱን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት አካላት እየሰሩ ይገኛሉ።