በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኳታር "ዶሃ ፎረም" በመካፈል ላይ ይገኛል

139

መጋቢት 18 ቀን 2014 (ኢዜአ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኳታር "ዶሃ ፎረም" በመካፈል ላይ ይገኛል።

የዶሃ ፎረም ዓለም አቀፋዊ የውይይት መድረክ ሲሆን ዘንድሮ "ወደ አዲሱ ዘመን ሽግግር" በሚል መሪ ሃሳብ ለ20ኛ ጊዜ እየተካሄደ ነው።

የዶሃ ፎረም እያጋጠሙ ባሉ ዓለምአቀፍ ይዘት ባላቸው ቁልፍ ፈተናዎች እና ወሳኝ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር ግልፅ አቅጣጫ እና ተግባር ተኮር ምክረ ሃሳቦችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የሚመራው ልዑክ ኢትዮጵያን በመወከል በፎረሙ ላይ እየተሳተፈ ሲሆን፤ በተመሳሳይ በመድረኩ የበርካታ ሃገራት መሪዎች ተካፋይ መሆናቸውን የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም