ቤተክርስቲያኗ በ135 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገንዘብ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ማቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አደረገች - ኢዜአ አማርኛ
ቤተክርስቲያኗ በ135 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገንዘብ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ማቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አደረገች
መጋቢት 16 ቀን 2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን 135 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገንዘብ በጦርነቱና በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አደረገች።
ፕሮጀክቱ በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋርና በኦሮሚያ ክልል በጦርነትና በጸጥታ መደፍረስ ችግር ላይ የወደቁ የማኅበረሰብ ክፍሎች መልሶ ለማቋቋም ይውላል ተብሏል።
በፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 227 ሺህ 555 ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 9 ሺህ 690 ህፃናት እንዲሁም 36 ሺህ 199 ደግሞ ተፈናቃዮች ይገኙበታል።
ለፕሮጀክቱ ጉዳት ለደረሰባቸውና ለተፈናቀሉ ወገኖች ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ እንደሚውልም ተገልጿል።