ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ቱርክ አደነቀች

መጋቢት 16 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን የቱርክ መንግስት አድንቋል።

የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ተከትሎ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ለዘላቂ ሰላምና ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የወሰነውን ቁርጠኛ ውሳኔ እንደሚያደንቅ ነው የቱርክ መንግስት ያስታወቀው።


የኢትዮጵያ መንግሰት ባደረገው ቁርጠኛ ውሳኔም የሰብዓዊ ድጋፍ ለትግራይ ክልልና ለሌሎችም አካባቢዎች በተሳለጠ ሁኔታ እንደሚደርስ እምነቱ መሆኑን አመልክቷል።


ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም