ቀጥታ፡

የአሸንዳ በዓልን በመዲናዋ ማክበራችን ከሌሎች የበዓሉ ተሳታፊዎች ጋር በፍቅርና በአንድነት እንድናከብር እድል ፈጥሮንናል---ወጣቶች

አዲስ አበባ ነሐሴ 29/2010 የአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ መከበሩ ከሌሎች የበዓሉ ተሳታፊዎች ጋር በፍቅርና በአንድነት እንዲሰባሰቡ እድል እንደፈጠረላቸው የበዓሉ ተሳታፊ ወጣቶች ገለጹ። ከነሐሴ አጋማሽ  ጀምሮ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሚከበረው የአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ ክብረ በዓል የመዝጊያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። ከሰሜን ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ወጣቶች ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባህል ማዕከል እስከ ስድስት ኪሎ የሚገኘው ሰማዕታት ሀውልት አደባባይ ባለው መንገድ ላይ ባህላዊ ጨዋታዎችን አሳይተዋል። የበዓሉ ተሳታፊ ወጣቶች ለኢዜአ እንደገለጹት በአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ በዓል የመዝጊያ መርሃ ግብር በመዲናዋ መካሄዱና በጎዳና ላይ ባህላዊ ጭፈራዎቹን ማሳየታቸው ለመዲናዋ ነዋሪዎች ቱባ ባህሉን ለማስተዋወቅ አስችሏቸዋል። ከሌሎች  የበዓሉ ተሳታፊዎች ጋርም በዓሉን በፍቅርና በደስታ ለማክበርና እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ ለማድረግም እድል እንደፈጠረላቸውም ገልጸዋል። ምንትዋብ አበበ ከደቡብ ጎንደር በዓሉ ነጻነትን የበለጠ እንደሚያጎላ ገልጻ የተሸለ የቱባ ባህሉን እያወጡ እንደሚያከብሩ እርግጠኛ መሆኗን ትናገራለች፡፡ የአሸንዳ በዓል የኢትዮጵያ ሀብት  ነው ያለው ሌላው ወጣት ወርቁ አስማረ ከማዕከላዊ ጎንደር በበዓሉ ብሔር ብሄረ ሰቦች ባህሎቻቸው ልምድ ለውሰድ አይኘጠኛ መንገድ ነው ብሏል፡፡ ወጣት አሰፉ አያልነህ ከዋግምራ በበኩሉ"ትልቅ ደስታ ነው የፈጠረልኝ ማለት እያንዳንዳችን ከተለያየ ቦታ መጥተን በአንድ ላይ ተደምረን በፍቅር ተዝናንተን ተጫውተን ያለንን ባህል አሳይተን ስለመጣን በጣም ትልቅ ደስታ ነው  የተሰማኝ ብሏል፡፡ ወጣቱ እንዳለው አሸንዳ ባህላችን ከድሮ ከጥንት ከትውልድ ትውልድ እየተወራረሰ የመጣና እኛ ደግሞ ከእናቶቻችን ተቀብለን የሚናስቀጥለው የጨዋታ ቅርሳችን ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከነሐሴ አጋማሽ አንስቶ የሚከበረው የአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ በዓል መክፈቻ ላይ በዓሉ "የሰሜን ኢትዮጵያ ህዝቦች የአንድነትና ወንድማማችነት ህያው ማስረጃ መሆኑን  መግለጻቸው ይታወሳል። በዓሉ የአንድ ክልል ወይም የኢትዮጵያ ሃብት ብቻ ሳይሆን የዓለም ጭምር መሆኑን በመገንዘብም በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በጋራ መስራት እንዳለብን ማሳሰባቸው እንዲሁ።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም