በህብረተሰብ የጤና አደጋ ቁጥጥር ላይ የሚመክር ሀገር አቀፍ ፎረም በሐረር ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
በህብረተሰብ የጤና አደጋ ቁጥጥር ላይ የሚመክር ሀገር አቀፍ ፎረም በሐረር ተጀመረ
ሐረር ፤ መጋቢት 15/2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2014 በጀት ዓመት ሁለተኛው የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ላይ የሚመክር ሀገር አቀፍ ፎረም ዛሬ በሐረር ከተማ ተጀመረ።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው ፎረሙ ባለፉት ሶስት ወራት በድርቅ እና ጦርነቱ በተጎዱ አካባቢዎች ከጤናው ዘርፍ አኳያ በተሰጠ ምላሽ ዙሪያ እንዲሁም ባለፉት ስድስት ወራት በህብረተሰብ ጤና ላይ የደረሰ ወረርሽኝ መከላከል ክንውን ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ተመልክቷል።
በፎረሙ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሰአረላ አብዱላሂ፣የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንዲሁም የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተደድሮች የጤና ቢሮ ሃላፊዎች እየተሳተፉ መሆኑን ኢዜአ ከሐረር ዘግቧል።