ቀጥታ፡

አቶ መስፍን ጣሰዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ ተሾሙ

መጋቢት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡

አቶ መስፍን ጣሰው በአየር መንገዱ ላለፉት 38 አመታት በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን አየር መንገዱ አሁን ያለበትን የስኬት ጎዳና ይበልጥ አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ተገልጿል።

አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም