ቀጥታ፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሚዛን አማን ከተማ ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሚዛን አማን ፣ መጋቢት 14/2014 (ኢዜአ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ህዝባዊ የውይይት መድረክ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።

መድረኩን እየመሩ ያሉት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳና ሌሎችም አመራሮች ናቸው።

በውይይቱ ላይ ከተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የህዝብ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው ።

ዶክተር ቢቂላ በመድረኩ መክፈቻ ላይ፤ በተለይ ኢትዮጵያ ለውጭ ኃይሎች አልበረከክ ባይነቷን ዳግም ለዓለም ማህበረሰብ ያሳየችበት የለውጥ ምዕራፍ ጉዞን ለማስቀጠል በየደረጃው የሚገኘው ህዝብ ሀሳቡን በነፃነት የሚገልጽበት መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም