በ18ኛው የቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ከዓለም የቀዳሚነት ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት አትሌቶችና የልዑኩ አባላት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
በ18ኛው የቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ከዓለም የቀዳሚነት ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት አትሌቶችና የልዑኩ አባላት አዲስ አበባ ገቡ
መጋቢት 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) በ18ኛው የቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ከዓለም የቀዳሚነት ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት አትሌቶችና የልዑኩ አባላት አዲስ አበባ ገቡ።
ልዑኩ አዲስ አበባ አየር ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊዎች በማርሽ ባንድአቀበባበል ተድርጎላቸዋል።
አትሌቶች ከአየር መንገድ ጀምሮ እስከ ሸራተን ሆቴል በክፍት መኪና ሆነው በሕዝብ አቀባበል ይደረግላቸዋል።
በሸራተን አዲስ ሆቴል የምስጋና እና የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት አሰጣጥ ይካሄዳል።
በአቀባበሉ ላይ የባህልና ስፓርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉን ጭምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ማግኘት የቻለች ሲሆን ውጤቱም የኢትዮጵያ የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር የምንጊዜም ከፍተኛ ውጤት ነው።