በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራ ልዑክ በማእከላዊ ጎንደር ዞን የበጋ መስኖ ልማትና የጎርጎራ ፕሮጀክትን እየጎበኘ ነው

109

መጋቢት 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራ የሚኒስትሮችና የክልል ርእሰ መስተዳደሮች ልዑካን ቡድን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ዋዋ ቀበሌ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትና የጎርጎራ ገበታ ለሃገር ፕሮጀክትን እየጎበኘ ነው።

በጉብኝቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መለስ መኮንን፣የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ፣የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው፣የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሃይለማርያም ከፍያለው በክልሉ በዘንድሮ የበጋ ወቅት በመስኖ በመታገዝ በስንዴ እየለማ ካለው 41 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ 2 ሚለዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

በክልሉ በበጋ መስኖ እየለማ ካለው መሬት 2 ሺህ 600 ሄክታሩ በማዕከላዊ ጎንደር የለማ መሆኑን ጠቁመው በዞኑ ከለማው መሬትም 100 ሺህ ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም