የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በጦር ሜዳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም አክሞ ሰው ማዳን እንደሚቻል በተግባር አሳይታችኋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በጦር ሜዳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም አክሞ ሰው ማዳን እንደሚቻል በተግባር አሳይታችኋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
መጋቢት 10 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች በጦር ሜዳ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም አክሞ ሰው ማዳን እንደሚቻል በተግባር አሳይታችኋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
በህግ ማስከበርና በህብረ ብሄራዊ አንድነት ዘመቻ ለተሳተፉ የህክምና ባለሙያዎች የእውቅና መርሐ ግብር እየተከናወነ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅት የህክምና ባለሙያዎች ግንባር ድረስ በመሄድ ጀግኖቻቸውን በማከም ኢትዮጵያን አድነዋል ብለዋል።
የህክምና ባለሙያዎች ጠላትና ወዳጅ ሳይለዩ የቆሰለውን ሁሉ በማከም የሰውነት ሚዛን መሆናቸውን እንዳሳዩም ገልጸዋል።
የሙያ ግዴታችሁን በማክበር ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን በተግባር አሳይታችኋል ብለዋል።
ካላቸው ቀንሰው ያስተማሯችሁን ኢትዮጵያውያንን ለመታደግ ላደረጋችሁት ጥረት በመንግሥትና በራሴ ስም ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።
የህክምና ባለሙያዎች በጦር ግንባር በአስቸጋሪ ሁኔታ ተገኝታችሁ የሰውን ህይወት አድናችኋል፣ በችግር ውስጥ ሆኖ የሰውን ህይወት ማዳን እንደሚቻልም አሳይታችኋል ሲሉም ገልጸዋል።
እየተካሄደ ባለው የእውቅና መርሐ ግብር ላይ ከጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የአገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ