የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ የኢትዮጵያ አየር ክልል አስተማማኝ ዘብ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ የኢትዮጵያ አየር ክልል አስተማማኝ ዘብ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ የአገር ሉአላዊነት አለኝታና የኢትዮጵያ አየር ክልል አስተማማኝ ዘብ መሆኑን የአየር ሃይሉ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለፁ።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፤ የተቋሙን አደረጃጀትና ያለበትን ወቅታዊ አቋም በማስመልከት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
አየር ሃይል አሁን ላይ በአቪዬሽንና በአየር መከላከያ ዘመኑ የተደረሰበትን ቴክኖሎጂ የሚጠቀምና በብቁ ባለሙያዎችም የተደራጀ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ በሰው ሃይል እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲሁም በትጥቅ የተደራጀ ሆኗል።
የኢትዮጵያን የአየር ክልል በመጠበቅ ሂደት ዘመናዊና አስተማማኝ መሆኑን ጠቅሰው ለግዳጅ አፈፃፀም ውጤታማነትም ከቴክኖሎጂው ጋር አብሮ የሚራመድ የሰው ሃይል መገንባቱን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ የአገር ሉአላዊነት አለኝታና የኢትዮጵያ አየር ክልል አስተማማኝ ዘብ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎችና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ተቋም ሆኗል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎችና በወጣቶች እየተገነባ ያለ ጠንካራ ተቋም መሆኑንም ሌተናል ጄነራል ይልማ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአገሪቱን የአየር ክልል ከመቆጣጠር ባሻገር ተልዕኮዎችን በከፍተኛ በፍጥነትና በውጤታማነት የሚያሳካ የአገር ኩራትና አለኝታ ሆኗል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በቀድሞው አጠራር ከታ ሜዳ አሁን ላይ ሀረር ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ1936 ዓ.ም እንደተመሰረተ መረጃዎች ይጠቁማሉ።