ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

70

መጋቢት 5 ቀን /2014 (ኢዜአ) ባለፈው ሳምንት 71.8 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው የኮንትሮባንድ እቃ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል 62.8 ሚሊዮን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃ እና 5.8 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ኮንትሮባንድ እቃ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዙን አስታውቋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃው በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በብርበራና በጥቆማ የተያዘ ነው ተብሏል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣መድሀኒት፣የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙበት ከኮሚሽኑ የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ 

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም