አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የወሎ ዩኒቨርሲቲን መልሶ ለማቋቋም የሚውል 33 ሚሊዮን ብር የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ

83

መጋቢት 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለወሎ ዩኒቨርሲቲ መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል 20 ሚሊዮን ብርና 13 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የአይነት ድጋፎችን አደረገ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት የተጎዱ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም 10 ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ በመሆን መልሶ ለማቋቋም  በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሥሩ ከሚገኙት ከሁሉም ኮሌጆች ያሰባሰብው 7 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የአይነት ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።

ድጋፉ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በዛሬው እለት ወደ ሥፍራው እንደሚያቀኑና 6 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ድጋፎችም በቀጣዮቹ ቀናት ወደ ሥፍራው እንደሚያመሩ ጠቁመዋል።

ዩኒቨርስቲው በገንዘብ ሚኒስትር በኩል ለወሎ ዪኒቨርስቲ ድጋፋ የሚውል 20 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ነው ፕሮፊሰር ጣሰው የገለጹት።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ድጋፉ ማደረጉ የወሎ ዩኒቨርስቲ መልሶ እንዲቋቋምና የመማር ማስተማሩ ሥራ በአግባቡ እንዲያከናውን እንደሚረዳውም ጠቁመዋል።

ይህም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ ጠቃሜታ እንዳለው ገልጸዋል።   

በሰሜኑ የአገሪቱ ጦርነት የወደሙ ተቋማት መልሶ የመገንባት ሂደቱ ወደ ቀድሞ ሥራቸው እስኪመለሱ ሁሉም ተቋማት የሚያደርጉት ድጋፍ አጠናከረው እንዲቀሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም