ቀጥታ፡

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ እንዲሆን ጉልህ ሚና ነበራቸው - ፓስተር ጻድቁ አብዶ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 03 ቀን 2014 (ኢዜአ) ብፁዑ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ እንዲሆን ጉልህ ሚና እንደነበራቸው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ ገለጹ።

በመስቀል አደባባይ በተከሄደው የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ አስክሬን ሽኝት መርሃ ግብር  የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ በብጹዕነታቸው እረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የጠብን ግድግዳ በማፍረስ ለአንድነትና መተሳሰብ ሲሉ ለፈጣሪያቸው ታምነው የእውነትን መንገድ ተከትለዋል ብለዋል።

በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በከንቱ የሚፈሰውን ደም በማስቆም ከጥፋት መንገድ መመለስ ይገባልም ነው ያሉት ፓስተር ጻዲቁ።

ከብጹዕነታቸውም የሰላምና ይቅርታን መንገድ በመማር ለአብሮነትና አንድነት ተባብሮ መስራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም