አባትን ማጣት ያሳዝናል፣ አባት ጥላና ከለላ ነው - ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 03 ቀን 2014 (ኢዜአ) አባትን ማጣት ያሳዝናል፣ አባት ጥላና ከለላ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን የሀዘን መልዕክት አስተላልፈዋል።

ካርዲናሉ በመልዕክታቸው ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ታላቅ አባት እንደነበሩ አስታውሰው፤ አሁንም ወደ ፈጣሪያቸው ሄደው ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ይጸልያሉ ብለዋል።

 አክለውም አባትን ማጣት ያሳዝናል፣ አባት ጥላና ከለላ ነው ሲሉ የሐዘን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ድርቅና የተለያዩ ችግሮች መኖራቸውን ገልጸው፤ ብጹዕነታቸው ይህን ለፈጣሪ ያሳስባሉ በማለትም ገልጸው ለብጹዕነታቸው ነፍስም ፈጣሪ ምህረት እንዲያደርግላቸው ተመኝተዋል።

ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ የስንብት መርሃ ግብር ላይ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም