በመዲናዋ ከ1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የመንገድ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው

56

የካቲት 27 ቀን 2014(ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ከ1ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን መርቀው እየከፈቱ ነው።

መንገዶቹ ከሃይሌ ጋርመንት _ጀሞ አደባባይ (አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መንገድ) ፣ የሲኤምሲ ሚካኤል ተሸጋጋሪ ድልድይ፣ የዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ -ለገሀር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትና ሌሎችን ያካትታል።

ከንቲባዋ ከራስ ደስታ ሆስፒታል እስከ ቀጨኔ መድኃኒያለም ድረስ የተገነባውን የአስፋልት ኮንክሪት መንገድንም መርቀው ከፍተዋል።

መንገዱ ከዚህ በፊት ጠባብ የነበረ ሲሆን 2 ነጥብ 5 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው መሆኑ ተነግሯል።

ለምረቃ ከበቁት ፕሮጀክቶች ውስጥ ስምንቱ በአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በኩል ቀሪዎቹ ደግሞ በስራ ተቋራጮች የተገነቡ ናቸው።

May be an image of road

የተመረቁት የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ 11 የአስፋልት መንገድ፣ 2 የመኪና ማቆሚያና የእግረኛ መንገድ ተካተዋል።

በአጠቃላይ ግንባታቸው ተጠናቆ በዛሬው እለት የተመረቁ መንገዶች በድምሩ ከ19 ኪሎሜትር በላይ ርዝመትና ከ13 እስከ 60 ሜትር የጎን ስፋት አላቸው።

መንገዶቹ አብዛኞቹ አዳዲስ በመሆናቸው የመንገድ መረቡን በማሳደግ የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ከማሳለጥ ባለፈ ለከተማዋ ውበት ያጎናጽፋሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም