ቀጥታ፡

የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰላም ግንባታና ግጭት አፍታት ዙሪያ ለሚያከናውነው ተግባር ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገለት

የካቲት 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) ስተርሊንግ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሰላም ግንባታና ግጭት አፍታት ዙሪያ ለሚያከናውነው ተግባር የሚውል ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እ.አ.አ በ2022/23 በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ሊሰራው ያሰበውን የሰላም ግንባታ፣ የግጭት አፈታትና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን የሚያጠናክር የበጀት ድጋፍ እንደተደረገለት የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ጉባኤው የበጀት ድጋፉን ያገኘው መቀመጫውን በአሜሪካ ዩታ ግዛት ካደረገው ስተርሊንግ ፋውንዴሽን ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑን ነው የገለጹት።

ጉባኤው እቅዱን ለመፈጸም የሀብት ማፈላለጊያ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል በማዘጋጀተ ለፋውንዴሽኑ የላከ ሲሆን ፋውንዴሽኑም ፕሮጀክቱን በመቀበል፣ የበጀት ድጋፍ ለማድረግ ፈቅዷል ነው ያሉት።

በዚህም መሠረት ጉባኤውና ፋውንዴሽኑ የድጋፍ ስምምነት ፊርማ ዛሬ በአሜሪካ ዮታ ግዛት አከናውነናል ብለዋል።

ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊትም ለጉባኤወ ልዩ ልዩ ድጋፎችን ሲያደርግ የነበረ ሲሆን በቅርቡም ለጉባኤው  ተሽከርካሪ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም