ኢዜአ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ትልቅ መረጃ አቅራቢ ነው - አምባሳደር ሰርጌይ ተረክሂን - ኢዜአ አማርኛ
ኢዜአ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ትልቅ መረጃ አቅራቢ ነው - አምባሳደር ሰርጌይ ተረክሂን
የካቲት 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ትልቅ መረጃ አቅራቢ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ሰርጌይ ተረክሂን ገለጹ።
አምባሳደሩ በመልዕክታቸው 80ኛ ዓመት የምስርታ በዓሉን እያከበረ ለሚገኘው ኢዜአ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተቋሙ በዛሬው ዕለት ባካሄደው የ80ኛ ዓመት ምስረታን የሚዘክር ዓውደ ርእይና የፓናል ውይይት ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተገኝተው መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል።
“ኢዜአ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ አህጉር ትልቅ መረጃ አቅራቢ ነው” ያሉት አምባሳደር ሰርጌይ ተረክሂን፤ በቀጣይ በፈጣን የመረጃ ፍሰት ውስጥ የመሪነት ቦታን በትክክል እንደሚይዝ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በአሁኑ ጊዜ ጥራት ያለው የመረጃ ይዘት ማምረት ለሁሉም የመገናኛ ብዙሃን ከባድ ስራ መሆኑን አመልክተዋል።
ኢዜአ ለአመታት ለኢትዮጵያውያን እና ለአለም አቀፍ ተመልካቾች አስተማማኝ የዜና ምንጭ ሆኖ እንደቆየም ገልጸዋል።
ለኢዜአ አመራሮችና ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እፈልጋለው ያሉት አምባሳደሩ፤ ኢዜአ በቀጣይ ተልዕኮውን የበለጠ እንዲያሳካ መልካም ምኞት ተምኝተዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼