" ዘመን ተሻጋሪ ምክሮች " መጽሐፍ ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
" ዘመን ተሻጋሪ ምክሮች " መጽሐፍ ተመረቀ
ጅማ ነሀሴ 27/2010 " ዘመን ተሻጋሪ ምክሮች " በሚል ርዕስ በጅማ ዩኒቨርስቲ መምህር የተዘጋጀ መጽሐፍ ዛሬ ተመርቆ ለንባብ በቃ፡፡ ደራሲው መምህር ቀነኔ ኢልያስ በምረቃው ስነስርዓት ወቅት በመጻሐፉ ውስጥ የተካተቱ ሃሳቦች ጊዜ የማያልፍባቸውና ሁሉንም የሚነኩ በመሆናቸው ዘመን ተሻጋሪ የሚል ርዕስ እንደሰጡት ተናግረዋል፡፡ መጽሐፉ አራት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎች እንዳሉት አመልክተው በእያንዳዳቸው ምዕራፍ ውስጥ አስራ ሁለት ዘላላማዊ ምክሮች ለሁሉም የሰው ልጆች የሚጠቅሙ በ300 ቃላት የተገለጹ ጠቃሚ ምክሮች እንዳተካተቱ ገልጸዋል፡፡ የሰው ልጅ ኑሮውን ለማሸነፍ እና አለም አሁን ካለችበት ደረጃ ለማድረስ ያደረገውን ትግል በዋነኛነት የሚያሳይ ነው መጸሐፉ፡፡ መጸሐፉን ለማዘጋጀት ከ25 ዓመታት በላይ እንደፈጀባቸው ጸሐፊው ጠቁመዋል፡፡ መጽሐፉን አሁን የታተመው በአማርኛና በአሮምኛ ቋንቋ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች ሶስት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ለማሳተም ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡ ወደ ስዊዲን ቋንቋ በማስተርጎም ለማሳተም በኢትዮጵያ የስዊድን ሰስቴነብል ድቭሎፕመንት አይሶሴሽን ፕሬዘዳንት ቱርቢየን ላካቲን በመጸሐፉ ምረቃ ስነስርዓት ወቅት ቃል ገብተዋል፡፡ በምረቃው ስነስርዓት ወቅት ከፌደራልና ከኦሮሚያ ባህል ቱሪዝም መስሪያ ቤት ፣ከጅማ ዩኒቨርስቲና ከአካባቢው የጻሐፊው ወዳጆችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡