ፓራዳይዝ ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅና ቢዝነስ ግሩፕ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ600 ኩንታል በላይ የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ

97

አዳማ፣ የካቲት 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) ፓራዳይዝ ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅና ቢዝነስ ግሩፕ በምዕራብ አርሲ ዞን በድርቅ ለተጎዱ የቆሬና ሻላ ወረዳዎች ከ600 ኩንታል በላይ የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ።

የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የአዳማ ካምፓስ ሠራተኞች፣ መምህራንና አመራሮች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የአይነት ድጋፍ ማድረጊያ ስነ ስርአት ዛሬ አካሂደዋል።

በወቅቱም ሠራተኞች፣ መምህራንና አመራሮች ደም ለግሰዋል።

የኮሌጁና ቢዝነስ ግሩፑ ባለቤት አቶ አየለ ኮሪሶ ለኢዜአ እንደገለጹት ዛሬ የተደረገውን ድጋፍ ዓይነት በተመሳሳይም በድርቅ ምክንያት ችግር ውስጥ ለሚገኙ የቦረና፣ ባሌና ጉጂ ዞኖች እስከ 1 ሺህ ኩንታል የሚደርስ የምግብ እህል ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጃታቸውን ተናግረዋል።

ከምግብ እህል ባለፈ የእንስሳት መኖ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አመላክተው፤ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ የአዳማ ካምፓስ ሠራተኞች፣ መምህራንና የማኔጅመንት አባላት ወገኖቻቸውን እንዲያግዙ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም