የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሕልውና ዘመቻው ጀብዱ ለፈፀሙ የሰራዊቱ አባላት የሜዳሊያ ሽልማት ሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሕልውና ዘመቻው ጀብዱ ለፈፀሙ የሰራዊቱ አባላት የሜዳሊያ ሽልማት ሰጠ
የካቲት 20/2014/ኢዜአ/ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሕልውና ዘመቻው ከፍተኛ ጀብዱ ለፈፀሙ የሰራዊቱ አባላት የሜዳሊያ ሽልማት እና ለከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ ማልበስ ስነ ስርዓት አካሄደ።
በመርሃ ግብሩ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሐኑ ጁላን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገኝተዋል።
በእለቱም በሕግ ማስከበርና በሕብረ ብሔራዊ ዘመቻው ከፍተኛ ሚና ለተጫወቱ አባላት ከመሸለም በተጨማሪ ለከፍተኛ መኮንኖች ማዕረግ የማልበስ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የአየር ኃይል ቴክኒሻኖችና የአየር ኃይል ኤር ፖሊስ አባላት ሰልጣኞች ተመርቀዋል።
በቢሾፍቱ የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ግቢ እየተከናወነ ባለው መርሃ ግብር የተሻለ የስራ አፈፃፀም ያሳዩና የስራ ጊዜያቸውን የጨረሱ የአየር ኃይል አባላትም የማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷቸዋል።