ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበራት ጥምረት ተመሠረተ

የካቲት 18 ቀን 2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበራት ጥምረት በይፋ ተመሠረተ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበራት ጥምረት የምስረታ ጉባኤውን ዛሬ አካሄዷል፡፡

በጉባኤው የመገናኛ ብዙኃን ማኅበራት ፕሬዝዳንቶች፣ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ የመገናኛ ብዙኃን ማኅበራት አባላት እና የዘርፉ አንጋፋ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

ጥምረቱ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበራት እንቅስቀሴን በተደራጀ መልኩ በመምራት የጋራ አቅም ለመፍጠር ያግዛል ተብሏል፡፡

ሙያዊ ስነ-ምግባርን ያከበሩ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚያግዝ እና በመገናኛ ብዙኃን ማኅበራቶች የሚታየውን የአሰራር እና የአደረጃጀት እንዲሁም የገለልተኝነት  ችግር በመቅረፍ ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረውም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም