ቀጥታ፡

በጉጂ ዞን ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጋ ንብርት ወደመ

ነገሌ የካቲት 18.2014 ዓ.ም (ኢዜአ) ከምእራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ 30 በርሜል ቤንዚል ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብርት መውደሙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በመምሪያው የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ሳጂን ፈየራ ከይረዲን ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው ትናንት ከቀኑ 11 ሰዓት የደረሰው ቤንዚል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በቡሌ ሆራ ዙሪያ ወረዳ በቀቻ ያአ ቀበሌ ሲደርስ ባጋጠመው የእሳት ቃጠሎ ነው፡፡

የታርጋ ቁጥር ኮድ3- 50169 አአ  የሆነ አይሱዙ የጭነት መኪናው ከከቡሌ ሆራ ከተማ አንድ የነዳጅ ማደያ 30 በርሜል ቤንዚን ጭኖ ወደ ዞኑ ሱሮ ከተማ ሲጓዝ የነበርው ተሽከርካሪ በእሳት በመያያዙ መሆኑን ገልጸዋል።

በአደጋው ተሽከርካሪው ከ20 በርሜል ቤንዚል ጋር ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ ሲወድም፤ ተሽከርካሪው ጥኖት ከነበረው ቤንዚል ውስጥ 10 በርሜል ቤንዚል በህብረተሰቡ ትብብር ከቃጠሎው መትረፉን ገተናግረዋል።

ዋና ሳጂን ፈየራ እንዳሉት ተሽከርካሪዎችን በህግ ከተፈቀደላቸው ውጭ መጠቀም ለአደጋ የሚያጋልጥ ስለሆነ ሁሉም ጥንቃቄ ማድረግ አለበት።

በተለይ ተቀጣጣይ ነገሮችን በህግ ከተፈቀደላቸው የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴዎች ውጭ መጫን ለመሰል አደጋ እንደሚያጋልጥ አንዱ ማሳያ በመሆኑ  ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል አስገንዝበዋል፡፡

ፖሊስ የእሳት አደጋውን መንስኤ ቤንዚል የጫነው መኪና መነሻና መድረሻ በምንና ለማን እንደሆነ በማጣራት ላይ መሆኑን ዋና ሳጂን ፈየራ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም