አሸናፊነትን ለማጽናት የሰላም ድል ያስፈልጋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

64

የካቲት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) አሸናፊነትን በዘላቂነት ለማጽናት የሰላም ድል እንደሚያሥፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

እስረኞችን ከመፍታትና ክስ ከማንሳት ጋር ተያይዞ ምላሽ ሲሰጡ የኢትዮጵያ ተጠቃሚነትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ዘርፈብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ታሳሪዎቹ ሲፈቱና ክሳቸው ሲቋረጥ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት፣ የታሳሪዎቹን ሁለንተናዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት እና ያገኘነውን ድል ለማጽናት ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ምክንያቱም ጦርነት አደገኛ ነገር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በእርስ በርስ ጦርነት ፍጹም ድል የሚባል ነገር የለም ሲሉም ነው የገለፁት፡፡

ጊዜያዊ ድል ደግሞ በውጊያ አሸንፎ ሌላኛው ወገን ሲበረታ ፈጽሞ መውደም እንደሆነ ነው ያነሱት፡፡

አሸናፊነትን ለማጽናት የሰላም ድል እንደሚያሥፈልግ ጠቅሰው፤ በሂደቱ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ ባለመሆንዋ ለአገር ዘላቂ ጥቅም ሲባል የሚወሰኑ ውሳኔዎችን መቃረን የለብንም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም