አዲስ ለተሾሙ እና ለነባር አምባሳደሮች ለቀጣይ ተልእኮ የሚያዘጋጅ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

60

የካቲት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ ለተሾሙ እና ለነባር አምባሳደሮች ለቀጣይ ተልእኮ የሚያዘጋጅ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

ስልጠናው ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እንዲሁም በአገር ገጽታ ግንባታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

ዲጂታል ዲፕሎማሲ እና የቆንጽላ አገልግሎትም ሌላኛው የስልጠናው ትኩረት መሆኑም ተገልጿል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አምባሳደሮቹ ከዓለም አቀፋ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር እኩል ለመራመድ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።

የሚሰጣቸውን ተልዕኮ የሚመጥን ውጤት ለማምጣት መዘጋጀት እንዳለባቸውም እንዲሁ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ሪፎርም ማድረጉን አንስተው፤ በዚህም ሚስዮኖች ጠንካራ የአቅም ምንጭ እንዲሆኑ የሚያስችል አደረጃጀት መሰራቱን ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪ ዲፕሎማሲውን ከአዳዲስ አሰራሮች ጋር በማጣጣም ውጤታማ ግንኙነት እንዲኖር መደረጉንም ነው የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም