ምክር ቤቱ የአገራዊ ምክክር እጩ ኮሚሽነሮችን ሹመት አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የአገራዊ ምክክር እጩ ኮሚሽነሮችን ሹመት አጸደቀ
አዲስ አበባ የካቲት 14/2014 (ኢዜአ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ ምክክር 11 እጩ ኮሚሽነሮችን ሹመት አጸደቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ያስችላል የተባለው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265 /2014 ማጽደቁ ይታወሳል።
በዚህም መሰረት አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን የሚመሩት 11 ኮሚሽነሮች ለመለየት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ የጥቆማ ዘዴዎች ከ600 በላይ ሰዎች ተጠቁመዋል።
ከተጠቆሙት ግለሰቦች መካከል 42ቱ አዋጁን መሰረት ተደርጎ መለየታቸውና ኅብረተሰቡም አስተያየት እንዲሰጣቸው መደረጉ ተገልፇል።
በመሆኑም አገራዊ ምክክሩን ለመምራት የ11 ዝርዝር ለምክር ቤቱ ቀርቦ ምክር ቤቱም ዛሬ ባካሄደው ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ በአምስት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ የኮሚሽሮቹን ሹመት አጽድቋል።
በዚህም መሰረት
ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ - ሰብሳቢ
ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ - ምክትል ሰብሳቢ
ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ
አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ
ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን
ዶክተር ዮናስ አዳዬ
አቶ ዘገየ አስፋው
አቶ መላኩ ወልደማሪያም
አምባሳደር መሃሙድ ድሪር
አቶ ሙሉጌታ አጎ እና
ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ ኮሚሽነሮች ሆነው ተሹመዋል።