ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እንድሪስ የህዳሴ ግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን አስመልክቶ የ'እንኳን ደስ አላችሁ' መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እንድሪስ የህዳሴ ግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን አስመልክቶ የ'እንኳን ደስ አላችሁ' መልዕክት አስተላለፉ
የካቲት 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን አስመልክቶ የ'እንኳን ደስ አላችሁ' መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ በግድቡ ግንባታ ሒደት ለተሳተፉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበው፤ የኢትዮጵያ መሪዎች በቅብብሎሽ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እውን እንዲሆን ማድረጋቸውንም ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡
ግድቡ ሃይል ማመንጨት እንዲጀምር አስተዋጽኦ ያበረከቱ ዜጎች ውለታ በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ለዘላለም በወርቅ ቀለም ታትሞ የኖራል ብለዋል፡፡
ከግድቡ የሚገኘውን ኃይል ለአገር ውስጥ ከመጠቀም ባለፈ ለጎረቤት አገራት ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ የእርስ በርስ ወዳጅንትን ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል።
ኢትዮጵያዊያን የግድቡ ግንባታ ሂደት እስኪጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼