ቀጥታ፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የ’እንኳን ደስ አለን’ መልእክት አስተላለፉ

የካቲት 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመር ምክንያት በማድረግ ለመላው ኢትዮጵያውያን የ’እንኳን ደስ አላቹህ’ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

“በንጉሡ ራዕይ ተጀመረ፣ ድፍረት ተከተለ፣ አስቀጣዮች መጡ፣ ግድባችን ኃይል አመነጨ! ያሉት ፕሬዚዳንቷ፤ ‘እንኳን ደስ አለን!’ ብለዋል።

"ሃሩርን ተጋፍጦ፣ ጤናውን እና ሕይወቱን ሠውቶ፣ የአገርን ጥቅም የሙጢኝ ይዞ ተደራድሮ፣ ካለው አካፍሎ፣ አገሬ ብሎ ለተነሣ ሁሉ ቀኑ የእናንተ ነው፣ እጅ እነሳለሁ” ሲሉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም