ቀጥታ፡

ሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የኢትዮጵያውያንን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚያበስር ነው

ሐረር የካቲት 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ኢትዮጵያውያን በአዲስ የብርሃንና የታሪክ ምዕራፍ ላይ መሆናቸውን የሚያበስር መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን አስመልክተው ለኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አለን! ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ኢትዮጵያውያን በአዲስ የብርሃንና የታሪክ ምዕራፍ ላይ መሆናቸውን የሚያበስር ነው ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው እንዳሉት ይህ አዲስ የታሪክ ምዕራፍና የብርሃን ብልጭታ ሀገራችን አሁን ካጋጠማት ውስብስብ ችግር ይልቅ መጪው ጊዜ የኢትዮጵያ ታላቅነት፣ ብልፅግና እና አንድነት ሀይል መሆኑን የሚያመላክት ነው።

በመሆኑም ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጀመር አንስቶ የሐረሪ ክልል ሕዝብን ጨምሮ መላው ኢትዮጵያውያን ፕሮጀክቱ እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ላደረጉት አስተዋጽኦ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያውያን በአንድነት የጀመሩትን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ በሕብረት ከዳር እንዲያደርሱት ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም