ሩሲያ የኤርትራ ወደብን የማልማት እቅድ እንዳላት አስታወቀች

33
ነሃሴ 26/2010 ሩሲያ በአፍሪካ ቀንድ የሎጀስቲክ ማዕከል ለማቋቋም የምታደርገውን ምክክር ተከትሎ የኤርትራ ወደብን የማልማት እቅድ እንዳላት አስታውቃለች፡፡ ራሽያ የኤርትራ ወደብን የማልማት እቅድ  እንዳላት ያስታወቀችው የሁለቱ ሃገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሩሲያ ሶቺ በተገናኙበት ወቅት ነው ፡፡ አፍሪካን ኒውስ ይዞት የወጣው ዘገባ እንዳመለከተው የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከኤርትራ አቻቸው ኡስማን ሳልህ ጋር በራሽያ ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ ላብሮቭ እንዳሉት የወደብ ልማት ፕሮጅክቱ የሁለቱን ሃገራት የንግድ ግንኙነት ያጠናክራል፡፡ “በተባበሩት መንግስታትና በሌሎችም አለም አቀፍ መድረኮች ከኤርትራ ጋር ላለን የቅርብ ትብብርና አቀራረብ እናመሰግናለን” ብለዋል ላቭሮቭ፡፡ የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና የፕሬዝዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ ከሃሙስ ጀምሮ በሩሲያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ባዛሬው እለት ቆይታቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ የኤርትራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እኤአ ሃምሌ 2018 ከኢትዮጵያ ጋር የሰላም ስምምነት ከፈረመች በኋላ እየተሻሻለ መምጣቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ የቀይ ባህር ዳርቻ ወደቦችን በጋራ ለማልማት ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን ባለፉት 20 አመታት በድንበር አቅራቢያ የነበረው ሰራዊታቸው ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለስ አድርገዋል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም