ባንኩ ያስገነባው አዲስ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይመረቃል - ኢዜአ አማርኛ
ባንኩ ያስገነባው አዲስ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይመረቃል
የካቲት 06 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስገነባው አዲስ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይመረቃል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የባንኩ ደንበኞች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አዲሱ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ከመሬት በላይ 209 ነጥብ 15 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን ፥ ባለ 53 ወለል ነው።
በውስጡ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ጨምሮ ሙዚየም እና ሲኒማ ቤትን ያካተተ ሲሆን፥ እስከ 1 ሺህ 500 መኪናዎችን መያዝ የሚችል ማቆሚያም አለው ተብሏል።