ቀጥታ፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ጅግጅጋ ገቡ

የካቲት 2/2014 (ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ጅግጅጋ ገቡ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማው በሚገኘው ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፍያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በዛሬው እለት በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረግ በሰመራ ከተማ አንድ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጡ የሚታወቅ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም